La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 14:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ ‘መምህሩ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው? ይላል፤’ በሉት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወደሚገባበት ቤትም ተከተሉት፤ የቤቱንም ጌታ፣ ‘መምህሩ፣ ከደቀ መዛሙርቴ ጋራ የፋሲካን እራት የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የትኛው ነው?’ ብሏል በሉት፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደሚገባበት ቤትም ተከተሉት፤ የቤቱንም ጌታ፥ መምህሩ፥ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር የፋሲካን ራት የምበላበት የእንግዳ ማረፊያ የትኛው ነው?” ብሏል በሉት፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደሚገባበትም ቤት ሂዱና የቤቱን ጌታ፥ ‘መምህር፥ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር የፋሲካን ራት የምበላበት ለእኔ የሚሆን የእንግዳ ማረፊያ ቤት የት ነው?’ ይላል በሉት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ተከተሉት፥ የሚገባበትንም የቤቱን ጌታ፦ መምህሩ፦ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ፋሲካን የምበላበት የእንግዳ ቤት ወዴት ነው? ይላል በሉት።

Ver Capítulo



ማርቆስ 14:14
8 Referencias Cruzadas  

እርሱም በመንገድ ሲወጣ አንድ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ተንበረከከለትና “ቸር መምህር ሆይ! የዘላለም ሕይወትን እወርስ ዘንድ ምን ላድርግ?” ብሎ ጠየቀው።


ማንም ‘ስለ ምን እንዲህ ታደርጋላችሁ?’ ቢላችሁ ‘ለጌታ ያስፈልገዋል፤’ በሉት፤ ወዲያውም ደግሞ ወደዚህ ይሰደዋል፤” አላቸው።


ከደቀ መዛሙርቱም ሁለት ላከ፤ እንዲህም አላቸው “ወደ ከተማ ሂዱ፤ ማድጋ ውኀ የተሸከመ ሰውም ይገናኛችኋል፤ተከተሉት።


እርሱም በደርብ ላይ ያለውን የተሰናዳና የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤በዚያም አሰናዱልን።”


የዚ​ያን ቤት ጌታ፦ መም​ህር ከደቀ መዛ​ሙ​ርቴ ጋር የፋ​ሲ​ካን በግ የም​በ​ላ​በት ቤት ወዴት ነው? ብሎ​ሃል በሉት።


ይህ​ንም ብላ ሄደች፤ እኅ​ቷን ማር​ያ​ም​ንም ቀስ ብላ ጠራ​ችና፥ “እነሆ፥ መም​ህ​ራ​ችን መጥቶ ይጠ​ራ​ሻል” አለ​ቻት።


እና​ንተ ‘መም​ህ​ራ​ችን፥ ጌታ​ች​ንም’ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካም ትላ​ላ​ችሁ፤ እኔ እን​ዲሁ ነኝና።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።