ማርቆስ 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይዘው ለፍርድ አሳልፈው በሚሰጧችሁ ጊዜ ሁሉ፣ በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ እንጂ ምን እንናገራለን በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተይዛችሁ ለፍርድ በምትቀርቡበት ጊዜ፥ በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ እንጂ ምን እንናገራለን በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች ይዘው ወደ ፍርድ ሲያቀርቡአችሁ፥ ‘ምን እንናገር ይሆን?’ በማለት አስቀድማችሁ አትጨነቁ፤ የሚናገረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ስለዚህ በዚያን ሰዓት የሚሰጣችሁን ብቻ ተናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲጐትቱአችሁና አሳልፈው ሲሰጡአችሁም ምን እንድትናገሩ አስቀድማችሁ አትጨነቁ፥ ዳሩ ግን በዚያች ሰዓት የሚሰጣችሁን ተናገሩ፤ የሚነግረው መንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እናንተ አይደላችሁምና። |
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል።
“እናንተ ግን ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤ ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፤ በምኵራብም ትገረፋላችሁ፤ ምስክርም ይሆንባቸው ዘንድ ስለ እኔ በገዥዎችና በነገሥታት ፊት ትቆማላችሁ።
ከዚህም ሁሉ አስቀድሞ ይይዙአችኋል፤ ወደ አደባባዮችም ይወስዱአችኋል፤ ያሳድዱአችኋል፤ ያስሩአችኋል፤ ስለ ስሜም ወደ ነገሥታትና ወደ መሳፍንት ይወስዱአችኋል።
ዮሐንስም መልሶ እንዲህ አለ፥ “ሰው ከሰማይ ካልተሰጠው በስተቀር እርሱ ራሱ ጸጋን ገንዘብ ሊያደርግ ምንም አይችልም።
ሁሉም መንፈስ ቅዱስን ተሞሉ፤ ይናገሩ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንደ አደላቸው መጠንም እየራሳቸው በሀገሩ ሁሉ ቋንቋ ይናገሩ ጀመሩ።
የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ፥ የአባቶቻችንም አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትን፥ እርሱም ሊተወው ወዶ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ልጁን ኢየሱስን ገለጠው።
ሲጸልዩም በአንድነት ተሰብስበው የነበሩበት ቦታ ተናወጠ፤ በሁሉም ላይ መንፈስ ቅዱስ መላባቸውና የእግዚአብሔርን ቃል በግልጥ አስተማሩ።
በእስጢፋኖስም ላይ መንፈስ ቅዱስ መላ፤ ወደ ሰማይም ተመለከተ፤ የእግዚአብሔርን ክብር፥ ኢየሱስም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየ።
ይህም ትምህርታችን ከሰው የተገኘ ትምህርት አይደለም፤ የአነጋገር ጥበብም አይደለም፤ መንፈስ ቅዱስ የገለጸው ትምህርት ነው እንጂ፤ መንፈሳዊ ጥበብም ከመንፈስ ቅዱስ የሚሆነውን መርምረው ለሚያውቁ ለመንፈሳውያን ነው።
ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።