በሰሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ፤ በሰገነቱ መውጫ እርከን ላይም ከእግሩ በታች አነጠፉት፥ መለከትም እየነፉ፥ “ኢዩ ነግሦአል” አሉ።
ማርቆስ 11:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፤ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፤ ተቀመጠበትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሶቻቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አምጥተው ልብሳቸውን በጀርባው ላይ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም የአህያውን ውርንጫ ወደ ኢየሱስ አመጡ፤ ልብሳቸውን በውርንጫው ጀርባ ላይ አድርገው ኢየሱስ ተቀመጠበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውርንጫውንም ወደ ኢየሱስ አመጡት፥ ልብሳቸውንም በላዩ ጣሉ፥ ተቀመጠበትም። |
በሰሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥነው ልብሳቸውን ወሰዱ፤ በሰገነቱ መውጫ እርከን ላይም ከእግሩ በታች አነጠፉት፥ መለከትም እየነፉ፥ “ኢዩ ነግሦአል” አሉ።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፣ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፣ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፣ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫንይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።