እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
ማርቆስ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስብከቱም፣ “እኔ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ፣ ከእኔ የሚበረታው ከእኔ በኋላ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስብከቱም፥ “እኔ ጐንበስ ብዬ የጫማውን ማሰሪያ መፍታት ከማይገባኝ፥ ከእኔ የሚበልጥ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም ይል ነበር፦ “የጫማውን ማሰሪያ ጐንበስ ብዬ ለመፍታት እንኳ የማልበቃ ከእኔ እጅግ የሚበልጥ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተጎንብሼ የጫማውን ጠፍር መፍታት የማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ በኋላዬ ይመጣል። |
እኔስ “ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
ዮሐንስም መልሶ ሁሉንም እንዲህ አላቸው፥ “እኔ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ግን የሚበልጠኝ የጫማውን ማሰሪያ እንኳ ልፈታለት የማይገባኝ ይመጣል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ፥ በእሳትም ያጠምቃችኋል።
ዮሐንስም መልእክቱን ሲፈጽም እንዲህ አላቸው፦ ‘እኔን ለምን ትጠራጠሩኛላችሁ? እርሱን አይደለሁም፤ የጫማውን ማዘቢያ ከእግሩ ልፈታ የማይገባኝ ከእኔ በኋላ እነሆ፥ ይመጣል።’
ጳውሎስም፥ “ዮሐንስ ከእርሱ በኋላ በሚመጣው በኢየሱስ ክርስቶስ እንዲያምኑ እየሰበከ የንስሓ ጥምቀትን አጠመቀ” አላቸው።
ተነሥታም በግንባርዋ በምድር ወድቃ ሰገደችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረድህ የጌታዬን ሎሌዎች እግር አጥብ ዘንድ አገልጋይ ነኝ” አለች።