ኤልሳዕም በሬዎቹን ተወ፤ ኤልያስንም ተከትሎ ሄደ፥ “አባቴንና እናቴን እስማቸው ዘንድ፥ እባክህ ተወኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። እርሱም“ሂድና ተመለስ፤ ምን አድርጌልሃለሁ?” አለው።
ማርቆስ 1:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዲያውም ጠራቸው፤ አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያውኑ ጠራቸው። እነርሱም አባታቸውን በጀልባው ላይ ከቅጥር ሠራተኞቹ ጋራ ትተው ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዲያውኑ ጠራቸው። እነርሱም ከቅጥር ሠራተኞቹ ጋር አባታቸውን በጀልባው ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወዲያውኑ ጠራቸው፤ እነርሱም አባታቸውን ዘብዴዎስን ከሠራተኞቹ ጋር በጀልባው ላይ ትተውት ኢየሱስን ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወዲያውም ጠራቸው አባታቸውንም ዘብዴዎስን ከሞያተኞቹ ጋር በታንኳ ላይ ትተው ተከትለውት ሄዱ። |
ኤልሳዕም በሬዎቹን ተወ፤ ኤልያስንም ተከትሎ ሄደ፥ “አባቴንና እናቴን እስማቸው ዘንድ፥ እባክህ ተወኝ፤ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። እርሱም“ሂድና ተመለስ፤ ምን አድርጌልሃለሁ?” አለው።
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ “እውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ፥
“ወደ እኔ የሚመጣ፥ ሊከተለኝም የሚወድ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።
እናቱንና አባቱን አላየኋችሁም ላለ፥ ወንድሞቹንም ላላወቀ፥ ልጆቹንም ላላስተዋለ፤ ቃልህን ለጠበቀ፥ በቃል ኪዳንህም ለተማጠነ።