ሉቃስ 9:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አላቸው፥ “በስሜ እንደዚህ ያለውን ሕፃን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል፤ ራሱን ከሁሉ ዝቅ የሚያደርግ እርሱ ታላቅ ይሆናል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላቸው፤ “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ማንም ቢኖር እኔን ይቀበላል፤ እኔን የሚቀበል ደግሞ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ከሁሉ ይበልጣልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ማንም ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን ይቀበላል፤ በእናንተ መካከል ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና፤” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል ሁሉ የላከኝን ይቀበላል። ከእናንተ መካከል ከሁላችሁም የሚያንስ እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ይሆናል፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን ይቀበላል፤ ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና አላቸው። |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ።
“እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም እንቢ የሚል እኔን እንቢ ይላል፤ እኔንም እንቢ የሚል የላከኝን እንቢ ይላል፤ እኔንም የሚሰማ የላከኝን ይሰማል።”
እውነት እላችኋለሁ፤ ሴቶች ከወለዱአቸው መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ ማንም አልተነሣም፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ግን የሚያንሰው ይበልጠዋል።”
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እኔ የምልከውን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።”
ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለ የሚጠብቀውም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”