ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፤ ተቀባም፤ ልብሱንም ለወጠ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እንጀራም አምጡልኝ አለ፤ በፊቱም እንጀራ አቀረቡለት፤ በላም።
ሉቃስ 7:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባችኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ራሴን ዘይት አልቀባህም፤ እርሷ ግን እግሮቼን ሽቱ ቀባች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርሷ ግን እግሬን ሽቶ ቀባች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ራሴን ዘይት እንኳ አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሮቼን ሽቶ ቀባች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንተ ራሴን ዘይት አልቀባኸኝም፤ እርስዋ ግን እግሬን ሽቱ ቀባች። |
ዳዊትም ከምድር ተነሥቶ ታጠበ፤ ተቀባም፤ ልብሱንም ለወጠ፤ ወደ እግዚአብሔርም ቤት ገብቶ ሰገደ። ወደ ቤቱም መጣ፦ እንጀራም አምጡልኝ አለ፤ በፊቱም እንጀራ አቀረቡለት፤ በላም።
ኢዮአብም ወደ ቴቁሔ ልኮ ከዚያ ብልሃተኛ ሴት አስመጣና፥ “አልቅሺ፤ የኀዘንም ልብስ ልበሺ፤ ዘይትም አትቀቢ፤ ስለ ሞተ ሰውም ብዙ ዘመን እንደምታለቅስ ሴት ሁኚ፤
ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፥ ወይራውንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፥ ወይኑንም ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።
አንተ ግን ስትጦም፥ በስውር ላለው አባትህ እንጂ እንደ ጦመኛ ለሰዎች እንዳትታይ ራስህን ተቀባ፤ ፊትህንም ታጠብ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል።
ስለዚህም እልሃለሁ፤ ብዙ ኀጢኣቷ ተሰርዮላታል፤ በብዙ ወድዳለችና፤ ጥቂት የሚወድድ ጥቂት ይሰረይለታል፤ ብዙ የሚወድድም ብዙ ይሰረይለታል።”