ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
ሉቃስ 7:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጥምቁ ዮሐንስ እህል ሳይበላ ወይንም ሳይጠጣ መጥቶ ነበርና ጋኔን አለበት አላችሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም መጥምቁ ዮሐንስ እህል ሳይበላና የወይን ጠጅ ሳይጠጣ ቢመጣ፣ ጋኔን አለበት አላችሁት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላ የወይን ጠጅም ሳይጠጣ መጥቶ ነበር፥ እናንተም “ጋኔን አለበት፤” አላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም መጥምቁ ዮሐንስ እህል ሳይበላና የወይን ጠጅም ሳይጠጣ ቢመጣ ‘ጋኔን አለበት፤’ አላችሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጥምቁ ዮሐንስ እንጀራ ሳይበላ የወይን ጠጅም ሳይጠጣ መጥቶ ነበርና፦ ጋኔን አለበት አላችሁት። |
ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው!
እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክርም መጠጥ ሁሉ አይጠጣም፤ ከእናቱ ማሕፀን ጀምሮም መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል።
በገበያ ተቀምጠው ባልንጀሮቻቸውን ጠርተው፥ “አቀነቀንላችሁ፥ አልዘፈናችሁምም፤ ሙሾም አወጣንላችሁ፥ አላለቀሳችሁምም የሚሉአቸው ልጆችን ይመስላሉ።
የሰው ልጅም እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እናንተ ግን እነሆ፥ በላተኛና ወይን ጠጪ ሰው፥ የኃጥኣንና የቀራጮች ወዳጅ አላችሁት።
አይሁድም እንዲህ አሉት፥ “አሁን ጋኔን እንዳለብህ ዐወቅን፤ አብርሃም ስንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ቃሌን የሚጠብቅ ለዘለዓለም ሞትን አይቀምስም ትላለህ።