ሉቃስ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጥተውም ይረዱአቸው ዘንድ በሌላ ታንኳ የነበሩትን ባልንጀሮቻቸውን ጠሩ፤ መጥተውም እስኪጠልቁ ድረስ ሁለቱን ታንኳዎች ሞሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሌላ ጀልባ የነበሩት ባልንጀሮቻቸው መጥተው እንዲያግዟቸውም በምልክት ጠሯቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱን ጀልባዎች በዓሣ ሞሏቸው፣ ጀልባዎቹም መስመጥ ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው በምልክት ጠሩአቸው፤ መጥተውም ሁለቱን ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በሌላይቱ ጀልባ ላይ የነበሩት ጓደኞቻቸው መጥተው እንዲያግዙአቸው በጥቅሻ ጠሩአቸው፤ እነርሱም መጥተው ሁለቱ ጀልባዎች ሊሰምጡ ጥቂት እስኪቀራቸው ድረስ በዓሣ ሞሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሌላ ታንኳም የነበሩትን ጓደኞቻቸውን መጥተው እንዲያግዙአቸው ጠቀሱ፤ መጥተውም ሁለቱ ታንኳዎች እስኪሰጥሙ ድረስ ሞሉአቸው። |
ስምዖን ጴጥሮስም ይህን አይቶ ከጌታችን ከኢየሱስ እግር በታች ሰገደና፥ “እኔ ኀጢአተኛ ሰው ነኝና አቤቱ ከእኔ ፈቀቅ በል፤” አለው።
ወንድሜና አጋዤ ስትሪካ ሆይ፥ እንድትረዳቸው አንተንም እለምንሃለሁ፤ ወንጌልን በማስተማር ከቀሌምንጦስና ሥራቸው ከተባበረ፥ ስማቸውም በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፈላቸው ከወንድሞቻችንም ሁሉ ጋር ከእኔም ጋር ደክመዋልና።