እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
ሉቃስ 5:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለምን በብዙ ይጾማሉ? ጸሎትስ ስለምን ያደርጋሉ? የፈሪሳውያን ወገኖች የሆኑትም ስለምን እንዲሁ ያደርጋሉ? ያንተ ደቀ መዛሙርት ግን ለምን ይበላሉ? ይጠጣሉም?” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አብዛኛውን ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተዎቹ ግን ይበላሉ፤ ይጠጣሉ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ ጸሎትም ያደርሳሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን፦ “የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ብዙ ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉም፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ሁልጊዜ የሚበሉትና የሚጠጡት ለምንድን ነው?” በማለት ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም፦ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ ምን ብዙ ይጦማሉ ጸሎትስ ስለ ምን ያደርጋሉ፥ ደግሞም የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ስለ ምን እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም? አሉት። |
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።
ከዚህም በኋላ በአንዲት ቦታ ጸለየ፤ ጸሎቱን በጨረሰ ጊዜም ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፥ “ጌታ ሆይ፥ ዮሐንስ ለደቀ መዛሙርቱ እንደ አስተማራቸው ጸሎት አስተምረን” አለው።
ሰማንያ አራት ዓመትም መበለት ሆና ኖረች፤ በጾምና በጸሎትም እያገለገለች፥ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አትወጣም ነበር።
ጌታም፥ “ተነሣና ቅን በምትባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ከጠርሴስ ሀገር የመጣ ሳውል የሚባል ሰው ፈልግ፤ እርሱ አሁን ይጸልያልና” አለው።