ሉቃስ 5:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዜናውም በሁሉ ተሰማ፤ ብዙ ሰዎችም ትምህርቱን ሊሰሙ፥ ከደዌአቸውም ሊፈወሱ ይመጡ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ ስለ እርሱ የሚወራው ወሬ ይበልጥ እየሰፋ ሄደ፤ እጅግ ብዙ ሰዎችም እርሱ የሚናገረውን ለመስማትና ካለባቸው ደዌ ለመፈወስ ይሰበሰቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ እርሱ የሚባለው ግን ይበልጡን በስፋት ተሰራጨ፤ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሱስ ዝና ግን ከምንጊዜውም ይበልጥ ተሰማ፤ ብዙ ሰዎችም እርሱን ለመስማትና ከበሽታቸውም ለመዳን ፈልገው ይሰበሰቡ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወሬው ግን አብዝቶ ወጣ፥ ብዙ ሕዝብም ሊሰሙትና ከደዌአቸው ሊፈወሱ ይሰበሰቡ ነበር፤ |
እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፤ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፤ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
በዚያን ጊዜም እጅግ ብዙ ሰዎች እርስ በርሳቸው እስኪረጋገጡ ድረስ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ ይላቸው ጀመረ፥ “አስቀድማችሁ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ፤ ይኸውም ግብዝነት ነው።