በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
ሉቃስ 4:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ገሊላ ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በገሊላ አውራጃ ወደምትገኘው ከተማ ወደ ቅፍርናሆም ወረደ፤ በዚያም በሰንበት ዕለት ሕዝቡን ያስተምር ጀመር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የገሊላ ከተማም ወደ ሆነችው ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ፥ ኢየሱስ በገሊላ ምድር ወደምትገኘው ከተማ ወደ ቅፍርናሆም ሄደ፤ በዚያም፥ ሕዝቡን በሰንበት ቀን ያስተምር ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ገሊላ ከተማም ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤ |
በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፤ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም።
እርሱም፥ “በውኑ ባለ መድኀኒት ራስህን አድን፤ በቅፍርናሆም ያደረግኸውንና የሰማነውን ሁሉ በዚህም በሀገርህ ደግሞ አድርግ ብላችሁ ይህችን ምሳሌ ትመስሉብኛላችሁ” አላቸው።
አይሁድ ግን እግዚአብሔርን የሚፈሩ የከበሩ ሴቶችንና የከተማውን ሽማግሌዎች አነሳሡአቸው፤ በጳውሎስና በበርናባስ ላይም ስደትን አስነሡ፤ ከሀገራቸውም አባረሩአቸው።