አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ በሥጋም በነበረበት ጊዜ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይሰጥ ፈጣሪህን አስብ።
ሉቃስ 24:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጄንና እግሬን እዩ፤ ዳስሱኝም፤ እኔ እንደ ሆንሁም ዕወቁ፤ በእኔ እንደምታዩት ለምትሐት አጥንትና ሥጋ የለውምና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጆቼንና እግሮቼን ተመልከቱ፤ እኔው ራሴ ነኝ። ደግሞም ንኩኝና እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና ዐጥንት የለውምና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ራሴ እንደሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ ዳስሱኝና እዩ፥ መንፈስ በእኔ እንደምታዩት፥ ሥጋና አጥንት የለውምና፤” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጆቼንና እግሮቼን አይታችሁ እኔ ራሴ መሆኔን ዕወቁ፤ ዳሳችሁም እዩኝ፤ በእኔ እንደምታዩት መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው። |
አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፥ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ በሥጋም በነበረበት ጊዜ መልካም ወይም ክፉ ቢሆን ስለ ሠራው ሁሉ መልስ ሳይሰጥ ፈጣሪህን አስብ።
እነርሱም በግንባራቸው ወድቀው፥ “የነፍስና የሥጋ ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ አንድ ሰው ኀጢአት ቢሠራ የእግዚአብሔር ቍጣ በማኅበሩ ላይ ይሆናልን?” አሉ።
ያንጊዜም ጌታችን ኢየሱስ ድምፁን ከፍ አድርጎ፥ “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በአንተ እጅ አደራ እሰጣለሁ” ብሎ ጮኸ፤ ይህንም ብሎ ነፍሱን ሰጠ።
ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፥ “ጌታችንን አየነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የችንካሩን ምልክት በእጁ ካላየሁ፥ ጣቴንም ወደ ተቸነከረበት ካልጨመርሁ፥ እጄንም ወደ ጎኑ ካላገባሁ አላምንም” አላቸው።
ከዚህም በኋላ ቶማስን፥ “ጣትህን ወዲህ አምጣና እጆችን እይ፤ እጅህንም አምጣና ወደ ጎኔ አግባ፤ እመን እንጂ ተጠራጣሪ አትሁን” አለው።
ሕማማትን ከተቀበለ በኋላ ብዙ ተአምራት በማሳየት አርባ ቀን ሙሉ እየተገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትም እየነገራቸውና እያስተማራቸው ሕያው ሆኖ ራሱንገለጠላቸው።
የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።
በሥጋ የወለዱን አባቶቻችን የሚቀጡን፥ እኛም የምንፈራቸው ከሆነ፥ እንግዲያ ይልቁን ለመንፈስ አባታችን ልንታዘዝና ልንገዛ በሕይወትም ልንኖር እንዴት ይገባን ይሆን?