ሉቃስ 24:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያቺንም ድንጋይ ከመቃብሩ ላይ ተንከባልላ አገኙአት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንጋዩም ከመቃብሩ ደጃፍ ተንከባልሎ አገኙት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንጋዩንም ከመቃብሩ ወዲያ ተንከባሎ አገኙት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቃብሩ የተዘጋበትን ድንጋይ ከመቃብሩ ወዲያ ተንከባሎ አገኙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥ |
ከሳምንቱም በመጀመሪያዪቱ ቀን ያዘጋጁትን ሽቶ ይዘው እጅግ ማልደው ወደ መቃብሩ ሄዱ፤ ሌሎች ሴቶችም አብረዋቸው ነበሩ።
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ በልቡ አዘነ፤ ወደ መቃብሩም ሄደ፤ መቃብሩም ዋሻ ነበር፤ በላዩም ታላቅ ድንጋይ ተገጥሞበት ነበር።
ድንጋዩንም አነሡ፤ ጌታችን ኢየሱስም ዐይኖቹን አቅንቶ እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰምተኸኛልና አመሰግንሃለሁ።