ሉቃስ 23:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሰቅሉትም ቃላቸውን ከፍ አድርገው እየጮሁ ለመኑ፤ ጩኸታቸውና የካህናት አለቆች ድምፅም በረታ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ በማድረግ እንዲሰቀል አጥብቀው ለመኑት፤ ጩኸታቸውም በረታ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጥብቀው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ድምፅ በረታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ግን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው “ስቀለው!” እያሉ ጮኹ፤ የሕዝቡና የካህናት አለቆች ድምፅ አየለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ግን እንዲሰቀል በታላቅ ድምፅ አጽንተው ለመኑት። የእነርሱ ጩኸትና የካህናት አለቆችም ቃል በረታ። |
ጲላጦስም ለሦስተኛ ጊዜ፥ “ምን ክፉ ነገር አደረገ? እነሆ፥ ለሞት የሚያበቃ ምክንያት አላገኘሁበትም፤ እንኪያስ ልግረፈውና ልተወው” አላቸው።