በሄዱም ጊዜ እንዳላቸው አገኙ፤ የፋሲካውንም በግ አዘጋጁ።
እነርሱም ሄደው ልክ ኢየሱስ እንደ ነገራቸው ሆኖ አገኙት፤ ፋሲካንም በዚያ አዘጋጁ።
ሄደውም እንዳላቸው አገኙና ፋሲካን አሰናዱ።
ሁለቱ ደቀ መዛሙርትም ሄደው፥ ሁሉ ነገር ልክ ኢየሱስ እንዳላቸው ሆኖ አገኙ፤ የፋሲካውንም ራት በዚያ አዘጋጁ።
የተላኩትም ሄደው እንደ አላቸው አገኙ።
ሰማይና ምድር ያልፋል፤ ቃሌ ግን አያልፍም።
እርሱም በሰገነት ላይ የተነጠፈ ታላቅ አዳራሽ ያሳያችኋል፤ በዚያ አዘጋጁልን።”
ሰዓቱም በደረሰ ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ በማዕድ ተቀመጠ፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርቱም ከእርሱ ጋር ተቀመጡ።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ብታምናስ የእግዚአብሔርን ክብር ታያለሽ አላልሁሽም ነበርን?” አላት።
እናቱም ለአሳላፊዎቹ፥ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው።
አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስት አድርጎ ይወርሰው ዘንድ ወዳለው ሀገር ለመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚደርስም ሳያውቅ ሄደ።