ሉቃስ 20:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጻፎችም ወገን የሆኑ ሰዎች፥ “መምህር ሆይ፥ መልካም ብለሃል” ብለው መለሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንድ ጸሐፍትም፣ “መምህር ሆይ፤ መልካም ተናገርህ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጻፎችም አንዳንዶቹ መልሰው “መምህር ሆይ! መልካም ተናገርህ፤” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕግ መምህራንም አንዳንዶቹ “መምህር ሆይ! መልካም ተናገርክ!” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጻፎችም አንዳንዶቹ መልሰው፦ መምህር ሆይ፥ መልካም ተናገርህ አሉት። |
ታላቅ ውካታም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑ ጸሐፍት ተነሥተው ይጣሉና ይከራከሩ ጀመሩ፤ “በዚህ ሰው ላይ ያገኘነው ክፉ ነገር የለም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት እንደ ሆነ እንጃ፥ ከእግዚአብሔር ጋር አንጣላ” አሉ።