ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፤ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
ሉቃስ 20:37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙታን እንደሚነሡስ እግዚአብሔር፦ ‘እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ’ ብሎ በቍጥቋጦው ዘንድ እንደ አነጋገረው ሙሴ ተናግሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ ስለ ቍጥቋጦ በተጻፈው ታሪክ ውስጥ ጌታን፣ ‘የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ፣ የያዕቆብ አምላክ’ በማለቱ ሙታን እንደሚነሡ ያሳያል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙታን እንደሚነሡ ግን ሙሴ እራሱ በቁጥቋጦው ታሪክ ጌታን ‘የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ’ በማለቱ አስታወቀ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ሙታን ትንሣኤ ግን፥ ሙሴ ስለ ቊጥቋጦው እሳት በተናገረው ታሪክ ውስጥ፥ ጌታን ‘የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብ አምላክ’ ብሎ ጠርቶታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙታን እንዲነሡ ግን ሙሴ ደግሞ በቍጥቋጦው ዘንድ ጌታን የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ በማለቱ አስታወቀ፤ |
ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል፥ ከአንተም በኋላ በዘርህ መካከል በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፤ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።
እነሆም፥ እግዚአብሔር በላዩ ቆሞበት ነበር፥ እንዲህም አለ፥ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ አትፍራ፥ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤
ያዕቆብም አለ፥ “የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፥ የአባቴ የይስሐቅ አምላክ ሆይ፥ ‘ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ፤ በጎነትንም አደርግልሃለሁ’ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ፥
ዳግመኛም እግዚአብሔር ሙሴን አለው፥ “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ትላለህ፦ የአባቶቻችሁ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ላከኝ፤ ይህ ለዘለዓለም ስሜ ነው፤ እስከ ልጅ ልጅ ድረስም መታሰቢያዬ ይህ ነው።
በየወቅቱም ከምድሪቱ ምላት፥ በቍጥቋጦው ውስጥ ከነበረው በረከት፥ በዮሴፍ ራስ ላይ፥ ከወንድሞቹም በከበረው በእርሱ ራስ ላይ ይውረድ።