ወንድሙን የሚበድለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአልን?” ብሎ ፈራ።
ሉቃስ 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህን በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንስ እንድታደርግ ማን ፈቀደልህ? እስኪ ንገረን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን እንደ ሆነ ንገረን፤ ሥልጣንስ የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እስኪ ንገረን፤ እነዚህን ነገሮች በምን ሥልጣን ነው የምታደርገው? ወይንስ ይህን ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” ብለው ተናገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “በል እስቲ ንገረን እነዚህን ነገሮች የምታደርገው በምን ሥልጣን ነው? ወይስ እነዚህን እንድታደርግ ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው?” ሲሉ ጠየቁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስኪ ንገረን፤ እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ ወይስ ይህን ሥልጣን የሰጠህ ማን ነው? ብለው ተናገሩት። |
ወንድሙን የሚበድለው ያም ሰው፥ “በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብፃዊውን ትናንት እንደ ገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?” አለው። ሙሴም፥ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአልን?” ብሎ ፈራ።
ከዚህም በኋላ በአንድ ቀን ሕዝቡን በመቅደስ ሲያስተምራቸው፥ ወንጌልንም ሲነግራቸው፥ የካህናት አለቆች፥ ጻፎችና ሽማግሌዎች ተነሡበት።
“እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ።