ጌታችን ኢየሱስም በእግዚአብሔር ዘንድ፥ በሰውም ዘንድ፥ በጥበብና በአካል በሞገስም አደገ።
ኢየሱስም በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት አደገ።
ኢየሱስም በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።
ኢየሱስ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት የተወደደ ሆኖ፥ በጥበብና በቁመት እያደገ ይሄድ ነበር።
ኢየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።
ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስ ቅዱስም ጸና፤ ለእስራኤልም እስከታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።
ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ጥበብንም የተመላ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበረች።
እንዲህ አድርጎ ለክርስቶስ የሚገዛ ግን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና በሰውም ዘንድ የተመረጠ ነው።
ብላቴናው ሳሙኤልም አደገ፤ በእግዚአብሔርም በሰውም ፊት ሞገስ እያገኘ ሄደ።