ሉቃስ 2:47 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰሙትም ሁሉ አስተዋይነቱንና አመላለሱን ያደንቁ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይደነቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሶቹ ተገረሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይገረሙ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ። |
ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፤ ብዙዎችም ሰምተው ተገረሙና “እነዚህን ነገሮች ይህ ከወዴት አገኛቸው? ለዚህ የተሰጠችው ጥበብ ምንድር ናት? በእጁም የሚደረጉ እንደነዚህ ያሉ ተአምራት ምንድር ናቸው?
ሁሉም የንግግሩን መከናወን መሰከሩለት፤ የአንደበቱንም ቅልጥፍና እያደነቁ፥ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።