ሉቃስ 19:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሦስተኛውም መጥቶ እንዲህ አለው፦ አቤቱ፥ በእኔ ዘንድ የነበረቺው ምናንህ እነኋት፤ በጨርቅ ጠቅልዬ አኑሬአት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌላውም አገልጋይ ቀርቦ እንዲህ አለው፤ ‘ጌታ ሆይ፤ በጨርቅ ጠቅልዬ ያቈየሁት ምናንህ ይኸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሌላውኛውም መጥቶ ‘ጌታ ሆይ! በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሌላውም አገልጋይ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ ‘ጌታዬ ሆይ! የሰጠኸኝ ገንዘብ ይኸውልህ፤ በጨርቅ ቋጥሬ አስቀምጬው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሌላውም መጥቶ፦ ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤ |
አንተ ያላኖርኸውን የምትወስድ፥ ያልዘራኸውን የምታጭድ፥ ያልበተንኸውንም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንህ ስለማውቅህ ፈርቼሃለሁና።
እነሆ፥ ምሳር በዛፎች ላይ ተቃጥቶአል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራውንም ዛፍ ሁሉ ይቈርጡታል፤ ወደ እሳትም ይጥሉታል።”
ሞቶ የነበረውም እንደ ተገነዘ፥ እጁንና እግሩንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰበን እንደ ተጠቀለለ ወጣ፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “እንግዲህስ ፍቱትና ተዉት ይሂድ” አላቸው።
በፍታዉንም በአንድ ወገን ተቀምጦ አየ፤ በራሱ ላይ የነበረው መጠምጠሚያም ሳይቃወስ ለብቻው ተጠቅልሎ አየ፤ ከበፍታዉ ጋርም አልነበረም።