La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሉቃስ 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም ሲሰሙ፤ ምሳሌ መስሎ ነገ​ራ​ቸው፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ቀርቦ ነበ​ርና፤ እነ​ር​ሱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወዲ​ያ​ውኑ የም​ት​ገ​ለጥ መስ​ሎ​አ​ቸው ነበ​ርና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕዝቡ ይህን እየሰሙ ሳሉ፣ በምሳሌ መናገሩን ቀጠለ፤ ምክንያቱም ወደ ኢየሩሳሌም በመቃረቡና ሰዎቹም የእግዚአብሔር መንግሥት የሚገለጥ ስለ መሰላቸው ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሳለ፥ ወደ ኢየሩሳሌም በመቃረቡ፥ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ እንደሚገለጥ ይገምቱ ነበርና፥ ተጨማሪ ምሳሌ ነገራቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰዎቹ ይህን በመስማት ላይ ሳሉ ኢየሱስ አንድ ምሳሌ ደግሞ ነገራቸው፤ እርሱ ወደ ኢየሩሳሌም ስለ ተቃረበ ሰዎቹ የእግዚአብሔር መንግሥት አሁኑኑ የምትገለጥ መስሎአቸው ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም ይህን ሲሰሙ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መቅረቡ ስለ ሆነ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ ሊገለጥ እንዳለው ስለ መሰላቸው ምሳሌ ጭምር ተናገረ።

Ver Capítulo



ሉቃስ 19:11
4 Referencias Cruzadas  

ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት መቼ ትመ​ጣ​ለች?” ብለው ጠየ​ቁት፤ እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት በመ​ጠ​ባ​በቅ አት​መ​ጣም።


የመ​ው​ጣቱ ወራ​ትም በቀ​ረበ ጊዜ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ለመ​ሄድ ፊቱን አቀና።


እነ​ር​ሱም ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉ፥ “ጌታ ሆይ፥ በዚህ ወራት ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መን​ግ​ሥ​ትን ትመ​ል​ሳ​ለ​ህን?” ብለው ጠየ​ቁት።