በእርሱም ዘመን የቤቴል ሰው አኪያል ኢያሪኮን ሠራ፤ በነዌም ልጅ በኢያሱ ቃል እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ በበኵር ልጁ በአቢሮን መሠረቷን አደረገ፥ በታናሹ ልጁም በዜጉብ በሮችዋን አቆመ።
ሉቃስ 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ ያልፍ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ገብቶ በዚያ ዐልፎ ይሄድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኢያሪኮም ገብቶ በዚያ በኩል አልፎ እየሄደ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ ወደ ኢያሪኮ ከተማ ገብቶ በዚያ በኩል አልፎ እየሄደ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ኢያሪኮም ገብቶ ያልፍ ነበር። እነሆም ዘኬዎስ የሚባል ሰው፥ እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ። |
በእርሱም ዘመን የቤቴል ሰው አኪያል ኢያሪኮን ሠራ፤ በነዌም ልጅ በኢያሱ ቃል እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል፥ በበኵር ልጁ በአቢሮን መሠረቷን አደረገ፥ በታናሹ ልጁም በዜጉብ በሮችዋን አቆመ።
ወደ ኢያሪኮም መጡ። ከደቀ መዛሙርቱና ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጣ የጤሜዎስ ልጅ ዕውሩ በርጤሜዎስ እየለመነ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ነበር።
የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ “ውጡና ምድሪቱን ኢያሪኮን እዩ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ጐልማሶች ሰላዮችን በስውር ላከ። እነዚያም ሁለት ጐልማሶች ሄዱ፤ ወደ ኢያሪኮም ደረሱ፤ ረዓብ ወደሚሉአትም ዘማ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ።