የሰሎሞንንም የማዕዱን መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
ሉቃስ 18:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፤ አንዱ ፈሪሳዊ፥ ሁለተኛውም ቀራጭ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ ቤተ መቅደስ ወጡ፣ አንዱ ፈሪሳዊ፣ ሌላው ቀረጥ ሰብሳቢ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ “ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፤ አንዱ ፈሪሳዊ ሌላውም ቀራጭ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሁለት ሰዎች ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ ሄዱ፤ አንዱ ፈሪሳዊ ሲሆን ሌላው ቀራጭ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህ ሲል፦ ሁለት ሰዎች ሊጸልዩ ወደ መቅደስ ወጡ፥ አንዱ ፈሪሳዊ ሁለተኛውም ቀራጭ። |
የሰሎሞንንም የማዕዱን መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም ሥርዐት፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያቀርበውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ተደነቀች።
ባሪያህና ሕዝብህ እስራኤል ወደዚህ ስፍራ የሚጸልዩትን ልመና ስማ፤ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ሰምተህም ይቅር በል።
“ተመልሰህ የሕዝቤን ንጉሥ ሕዝቅያስን እንዲህ በለው፦ የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጸሎትህን ሰምቻለሁ፥ እንባህንም አይቻለሁ፤ እነሆ፥ እኔ እፈውስሃለሁ፤ እስከ ሦስት ቀንም ድረስ ወደ እግዚአብሔር ቤት ትወጣለህ።
ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፥ “እግዚአብሔር እንዲፈውሰኝ፥ እኔስ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንድወጣ ምልክቱ ምንድን ነው?” አለው።
በስምንተኛው ቀን የተገዘርሁ፥ ከእስራኤል ሕዝብ ከብንያም ነገድ ከዕብራውያን ዕብራዊ ነኝ፤ በኦሪትም ፈሪሳዊ ነበርሁ።