ስለዚህም ነገር ሊመልሱለት አልተቻላቸውም።
እነርሱም ለዚህ አንዳች መልስ ሊያገኙ አልቻሉም።
ስለዚህ ነገርም ሊመልሱለት አልተቻላቸውም።
እነርሱ ግን ምንም መልስ መስጠት አልቻሉም።
አንድም ቃል ስንኳ ይመልስለት ዘንድ የተቻለው የለም፤ ከዚያ ቀንም ጀምሮ ወደ ፊት ማንም ሊጠይቀው አልደፈረም።
ይህንም ባለ ጊዜ በእርሱ ላይ በጠላትነት የተነሡበት ሁሉ አፈሩ፤ ነገር ግን ሕዝቡ ሁሉ ከእርሱ ስለሚደረገው ድንቅ ነገር ሁሉ ደስ አላቸው።
በሕዝቡም ሁሉ ፊት በአነጋገሩ ማሳሳት ተሳናቸው፤ መልሱንም አድንቀው ዝም አሉ።
ከዚያ ወዲህ ግን ሊጠይቀው የደፈረ ማንም የለም።
በእናንተ ላይ የሚነሡ ሊመልሱላችሁና ሊከራከሯችሁ እንዳይችሉ እኔ አፍንና ጥበብን እሰጣችኋለሁ።
ነገር ግን ይቃወሙት ዘንድ አልቻሉም፤ በጥበብና በመንፈስ ቅዱስ ይከራከራቸው ነበርና።