ሉቃስ 14:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያለዚያ ግን፥ ገና በሩቁ ሳለ አማላጆች መልእክተኞችን ልኮ ዕርቅ ይለምናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መቋቋም የማይችል ከሆነ፣ ሌላው ንጉሥ ገና ሩቅ ሳለ፣ መልእክተኞች ልኮ ዕርቅ ይጠይቃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካልሆነም ሌላው ገና ሩቅ ሳለ መልእክተኞች ልኮ ዕርቅ ይለምናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የማይችል ከሆነ ግን ሊወጋው የሚመጣው ንጉሥ ገና በሩቅ ሳለ ይህ ንጉሥ የሰላም መልእክተኞችን ወደ እርሱ ልኮ ዕርቅ ይጠይቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባይሆንስ ሌላው ገና ሩቅ ሳለ መልክተኞች ልኮ ዕርቅ ይለምናል። |
ከባለጋራህ ጋር ወደ ሹም በምትሄድበት ጊዜ ወደ ዳኛ እንዳይወስድህ በመንገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳህንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎሌው አሳልፎ ይሰጥሃልና። ሎሌውም በወኅኒ ቤት ያስርሃል።
ንጉሥም ሌላውን ንጉሥ ይወጋ ዘንድ ሊሄድ ቢወድ ሁለት እልፍ ይዞ ወደ እርሱ የሚመጣውን በአንድ እልፍ ሊዋጋው ይችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ይመክር የለምን?
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ወገን ከሁሉ ያልወጣ፥ የእርሱ ገንዘብ ከሆነውም ሁሉ ያልተለየ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ሄሮድስም በጢሮስና በሲዶና ሰዎች ተቈጥቶ ነበር፤ በአንድነትም ወደ እርሱ መጥተው የንጉሡን ቢትወደድ በላስጦስን እንዲያስታርቃቸው ማለዱት፤ የሀገራቸው ምግብ ከንጉሥ ሄርድስ ነበርና።