ሉቃስ 14:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእናንተም ወገን የግንብ ቤት መሥራት የሚወድ ቢኖር ይጨርሰው ዘንድ የሚችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የሚፈጅበትን የማያስብ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከእናንተ አንድ ሰው ሕንጻ ለመሥራት ቢፈልግ፣ መደምደም መቻል አለመቻሉን በመጀመሪያ ተቀምጦ ዋጋውን የማይተምን ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ እንዳለው አስቀድሞ ተቀምጦ ወጪውን የማይቈጥር ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከእናንተ መካከል አንዱ ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለሥራው ማስፈጸሚያ ምን ያኽል ገንዘብ እንደሚያስፈልገው አስቀድሞ የማያስብ ማነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ከሳራውን የማይቈጥር ማን ነው? |
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ወገን ከሁሉ ያልወጣ፥ የእርሱ ገንዘብ ከሆነውም ሁሉ ያልተለየ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ጳውሎስ ግን መልሶ፥ “ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ? እያለቀሳችሁ ልቤን ትሰብሩታላችሁ፤ እኔ እኮ ተስፋ የማደርገው መከራንና እግር ብረትን ብቻ አይደለም፤ እኔ ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በኢየሩሳሌም ለመሞትም ቢሆን የቈረጥሁ ነኝ” አለ።