ሉቃስ 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምስት ወፎች በሁለት ሻሚ መሐለቅ ይሸጡ የለምን? ከእነርሱ አንዲቱ ስንኳን በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐምስት ድንቢጦች በዐሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ይሁን እንጂ ከእነርሱ አንዲቷ እንኳ በእግዚአብሔር ዘንድ አትዘነጋም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አምስት ድንቢጦች በዐሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱ አንዲቱ ስንኳ በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምስት ድንቢጦች በዐሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱ አንድዋ እንኳ በእግዚአብሔር ፊት የተረሳች አይደለችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምስት ድንቢጦች በአሥር ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ስንኳ በእግዚአብሔር ፊት አትረሳም። |
የማይዘሩትንና የማያጭዱትን፥ ጎተራና ጕድጓድ የሌላቸውን የቍራዎችን ጫጭቶች ተመልከቱ፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል፤ እንግዲህ እናንተ ከወፎች እንዴት እጅግ አትበልጡም?
እነሆ፥ አበባዎችን እንደሚያድጉ ተመልከቱ፤ አይፈትሉም፤ አይደክሙም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በክብሩ ዘመን ሁሉ ከእነርሱ እንደ አንዱ አልለበሰም።