ሉቃስ 12:58 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባለጋራህ ጋር ወደ ሹም በምትሄድበት ጊዜ ወደ ዳኛ እንዳይወስድህ በመንገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳህንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎሌው አሳልፎ ይሰጥሃልና። ሎሌውም በወኅኒ ቤት ያስርሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከባላጋራህ ጋራ ወደ ዳኛ ፊት ለመቅረብ ስትሄድ፣ ገና በመንገድ ላይ ሳለህ ለመታረቅ ጥረት አድርግ፤ አለዚያ ጐትቶ ወደ ዳኛው ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለመኰንኑ አሳልፎ ይሰጥሃል፤ መኰንኑም ወደ ወህኒ ይጥልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ለመታረቅ ትጋ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባላጋራህ ከሶህ ወደ ፍርድ ቤት በሚወስድህ ጊዜ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ለመስማማት ተጣጣር፤ አለበለዚያ እርሱ ወደ ዳኛ ጐትቶ ይወስድሃል፤ ዳኛውም ለአሳሪው አሳልፎ ይሰጥሃል፤ አሳሪውም ወደ እስር ቤት ያገባሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባላጋራህ ጋር ወደ ሹም ብትሄድ፥ ወደ ዳኛ እንዳይጐትትህ ዳኛውም ለሎሌው አሳልፎ እንዳይሰጥህ ሎሌውም በወኅኒ እንዳይጥልህ፥ ገና በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ እንድትታረቅ ትጋ። |
ወዳጆች ሆይ! ስለምንካፈለው ስለ መዳናችን ልጽፍላችሁ እጅግ ተግቼ ሳለሁ፥ ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።