አንተንም የበደሉህን ሕዝብህን ፥ በአንተም ላይ ያደረጉትን በደላቸውን ሁሉ ይቅር በል፤ ይራሩላቸውም ዘንድ በማረኩአቸው ፊት ምሕረትን ስጣቸው፤
ሉቃስ 10:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንድ ሳምራዊ ግን በዚያች መንገድ ሲሄድ አገኘው፤ አይቶም አዘነለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሳምራዊ ግን እግረ መንገዱን ሲሄድ ሰውየው ወዳለበት ቦታ ደረሰ፤ ባየውም ጊዜ ዐዘነለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንድ ሳምራዊ ግን በጉዞ ላይ ሳለ እርሱ ወደ ነበረበት መጣ አይቶትም አዘነለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሳምራዊ ግን በዚያ በኩል ሲያልፍ ወደ ሰውየው መጣ፤ ባየውም ጊዜ ራራለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንድ ሳምራዊ ግን ሲሄድ ወደ እርሱ መጣ አይቶትም አዘነለት፥ |
አንተንም የበደሉህን ሕዝብህን ፥ በአንተም ላይ ያደረጉትን በደላቸውን ሁሉ ይቅር በል፤ ይራሩላቸውም ዘንድ በማረኩአቸው ፊት ምሕረትን ስጣቸው፤
ሣጥኑን በከፈተችም ጊዜ ሕፃኑን አየች፤ እነሆም፥ ሕፃኑ በሣጥኑ ውስጥ ያለቅስ ነበር፤ የፈርዖንም ልጅ አዘነችለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕብራውያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።
ወደ እርሱም ቀረበ፤ ቍስሉንም አጋጥሞ አሰረለት፤ በቍስሉ ላይም ወይንና ዘይት ጨመረለት፤ በአህያውም ላይ አስቀምጦ እንዲፈውሰው የእንግዶችን ቤት ወደሚጠብቀው ወሰደው፤ የሚድንበትንም ዐሰበ።
ያቺ የሰማርያ ሴትም፥ “አንተ አይሁዳዊ ስትሆን፥ እኔም ሳምራዊት ስሆን እንዴት ከእኔ ዘንድ ውኃ ልትጠጣ ትለምናለህ?” አለችው፤ አይሁድ ከሳምራውያን ጋር በሥርዐት አይተባበሩም ነበርና።