የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ለቅድስተ ቅዱሳን የተቀደሰ ይሆን ዘንድ ተመረጠ፤ እርሱና ልጆቹ ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ፊት ያጥኑና ያገለግሉ ነበር፤ በስሙም ለዘለዓለም ይባርኩ ነበር።
ሉቃስ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናት እንደሚያደርጉት የሚያጥንበት ጊዜ ደረሰ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሥርዐተ ክህነቱ መሠረት፣ ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን በዕጣ ተመረጠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ካህናት አሠራር ልማድ ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን ለማጠን ዕጣ ደረሰው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ካህናት ሥርዓት ወደ ጌታ ቤተ መቅደስ ገብቶ ለማጠን ዕጣ ደረሰበት። |
የእንበረም ልጆች አሮንና ሙሴ ነበሩ፤ አሮንም ለቅድስተ ቅዱሳን የተቀደሰ ይሆን ዘንድ ተመረጠ፤ እርሱና ልጆቹ ለዘለዓለም በእግዚአብሔር ፊት ያጥኑና ያገለግሉ ነበር፤ በስሙም ለዘለዓለም ይባርኩ ነበር።
አሮንና ልጆቹ ግን የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እንዳዘዘው ሁሉ ለቅድስተ ቅዱሳን ሥራ ሁሉ ስለ እስራኤልም ያስተሰርይ ዘንድ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ ይሠዉ ነበር፥ በዕጣኑም መሠዊያ ላይ ያጥኑ ነበር።
ነገር ግን በበረታ ጊዜ ለጥፋት ልቡ ታበየ፤ አምላኩንም እግዚአብሔርን በደለ፤ በዕጣን መሠዊያውም ላይ ያጥን ዘንድ ወደ መቅደስ ገባ።
አሁንም በፊቱ ትቆሙና ታገለግሉት ዘንድ፥ አገልጋዮቹም ትሆኑ ዘንድ፥ ታጥኑለትም ዘንድ እግዚአብሔር መርጦአችኋልና ቸል አትበሉ።”
እንደ ቆሬና ከእርሱም ጋር እንደ ተቃወሙት ሰዎች እንዳይሆን፥ ከአሮን ልጆች ያልሆነ ሌላ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ዕጣን ያጥን ዘንድ እንዳይቀርብ፥ እግዚአብሔር በሙሴ ቃል እንደ ተናገረው፥ ለእስራኤል ልጆች መታሰቢያ አደረጋቸው።
ሥርዐቱ፥ ዝግጅቱም እንዲህ ነበር፤ በመጀመሪያዪቱም ድንኳን በየጊዜው አገልግሎታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ፥ ካህናት ዘወትር ይገቡ ነበር።
ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ ካህን ይሆነኝ ዘንድ፥ በመሠዊያዬም ላይ ይሠዋ ዘንድ፥ ዕጣንንም ያጥን ዘንድ፥ ኤፉድንም በፊቴ ይለብስ ዘንድ፥ የአባትህን ቤት ለእኔ መረጥሁት፤ የእስራኤልንም ልጆች የእሳት ቍርባን ሁሉ ስለ ምግብ ለአባትህ ቤት ሰጠሁ።