La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 8:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ሮ​ን​ንም ልጆች አቀ​ረበ፤ ሙሴም የቀኝ ጆሮ​አ​ቸ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃ​ቸ​ው​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም አውራ ጣት ከደሙ ቀባ፤ ሙሴም ደሙን በመ​ሠ​ዊ​ያው ዙሪያ ረጨ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የአሮንንም ልጆች ወደ ፊት ጠራ፤ ሙሴም ከደሙ ጥቂት ወስዶ የቀኝ ጆሯቸውን ጫፍ፣ የቀኝ እጃቸውን አውራ ጣትና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት አስነካ፤ የቀረውንም ደም በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአሮንንም ልጆች አቀረበ፤ ሙሴም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግራቸውንም አውራ ጣት ከደሙ አስነካ፤ ሙሴም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ረጨ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ቀጥሎም የአሮንን ልጆች ወደ ፊት አቅርቦ የቀኝ ጆሮዎቻቸውን ጫፎች፥ የቀኝ እጆቻቸውን አውራ ጣቶችና የቀኝ እግሮቻቸውን አውራ ጣቶች ቀባ፤ ከዚህ የተረፈውንም ደም ሙሴ በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአሮንንም ልጆች አቀረበ፤ ሙሴም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀን እጃቸውንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግራቸውንም አውራ ጣት ከደሙ አስነካ፤ ሙሴም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ረጨ።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 8:24
4 Referencias Cruzadas  

አው​ራ​ው​ንም በግ ታር​ደ​ዋ​ለህ፤ ደሙ​ንም ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የአ​ሮ​ን​ንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንና የቀኝ እግ​ሩን አውራ ጣት ጫፍ፥ የል​ጆ​ቹ​ንም የቀኝ ጆሮ​አ​ቸ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃ​ቸ​ው​ንና የቀኝ እግ​ራ​ቸ​ውን አውራ ጣት ታስ​ነ​ካ​ለህ፤ ደሙ​ንም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ትረ​ጨ​ዋ​ለህ።


ካህ​ኑም ከበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ የሚ​ነ​ጻ​ውን ሰው የቀኝ ጆሮ​ውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁ​ንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግ​ሩ​ንም አውራ ጣት ይቀ​ባ​ዋል።


ስቡ​ንና ላቱን፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ ስባ​ቸ​ው​ንም፥ ቀኝ ወር​ቹ​ንም ወሰደ፤