ዘሌዋውያን 26:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰንበታቴንም ጠብቁ፤ የቀደስኋቸውንም ፍሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ሰንበታቴን ጠብቁ፤ መቅደሴንም አክብሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰንበታቴን ጠብቁ፥ ለመቅደሴም ክብርን ስጡ፤ እኔ ጌታ ነኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰንበቶቼን ጠብቁ፤ መቅደሴን አክብሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰንበታቴን ጠብቁ፥ መቅደሴንም ፍሩ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። |
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጃችሁ ምልክት ነውና ሰንበቴን ፈጽሞ ጠብቁ።