ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
ዘሌዋውያን 25:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሸጠ በኋላ መቤዠት ይችላል፤ ከወንድሞቹ አንዱ ይቤዠው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተሸጠ በኋላ ሊዋጅ ይችላል። ከዘመዶቹም አንዱ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተሸጠ በኋላ መቤዠት ይችላል፤ ከወንድሞቹ አንዱ ይቤዠው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተሸጠም በኋላ እንደገና ተዋጅቶ የመመለስ መብት አለው፤ ስለዚህም ከወንድሞቹ አንዱ ሊዋጀው ይችላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተሸጠ በኋላ መቤዠት ይችላል፤ ከወንድሞቹ አንዱ ይቤዠው፤ |
ከነቢያትም ልጆች የአንዱ ሚስት የሆነች አንዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪያህ ሞቶአል፤ ባሪያህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታውቃለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆቼን ባሪያዎች አድርጎ ሊወስዳቸው መጥቶአል” ብላ ወደ ኤልሳዕ ጮኸች።
አሁንም ሥጋችን እንደ ወንድሞቻችን ሥጋ፥ ልጆቻችንም እንደ ልጆቻቸው ናቸው፤ እነሆም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችን ባሪያዎች ይሆኑ ዘንድ ሰጥተናል፤ ከሴቶችም ልጆቻችን ባሪያዎች ሆነው የሚኖሩ አሉ፤ ታላላቆችም እርሻችንንና ወይናችንን ይዘዋልና ልናድናቸው አንችልም” የሚሉ ነበሩ።
እኔም፥ “ለአሕዛብ የተሸጡትን ወንድሞቻችንን አይሁድን በፈቃዳችን ተቤዠን፤ እናንተስ ወንድሞቻችሁን ትሸጣላችሁን? እነርሱስ ለእኛ የተሸጡ ይሆናሉን?” አልኋቸው። እነርሱም ዝም አሉ፤ መልስም አላገኙም።
“ከአንተ ጋር ያለው ወንድምህ ቢደኸይ፥ እጁም በአንተ ዘንድ ቢደክም እንደ እንግዳና እንደ መጻተኛ ትረዳዋለህ፤ ከአንተም ጋር ይኑር።
“በአንተም ዘንድ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆን፥ ወንድምህም በእርሱ አጠገብ ቢደኸይ፥ ራሱንም ለመጻተኛው፥ ወይም ለእንግዳው ወይም ለወገኖቹ ዘር ቢሸጥ፥
ወይም አጎቱ ወይም የአጎቱ ልጅ ይቤዠው፤ ወይም ከወገኑ ለእርሱ የቀረበ ዘመድ ይቤዠው፤ ወይም እርሱ እጁ ቢረጥብ ራሱን ይቤዠው።