ዘሌዋውያን 25:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ዓመት እርሻህን ትዘራለህ፤ ስድስት ዓመትም ወይንህን ትቈርጣለህ፤ ፍሬዋንም ትሰበስባለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስት ዓመት በዕርሻህ ላይ ዝራ፤ ስድስት ዓመት ወይንህን ግረዝ፤ ፍሬውንም ሰብስብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስት ዓመት እርሻህን ትዘራለህ፥ ስድስት ዓመትም የወይን ተክልህን ግረዝ ፍሬዋንም ሰብስብ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ዘርህን ትዘራለህ፤ የወይን ተክልህን ትገርዛለህ፤ እህልህን ትሰበስባለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስት ዓመት እርሻህን ዝራ፥ ስድስት ዓመትም ወይንህን ቍረጥ ፍሬዋንም አግባ። |
በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት፤ አሳርፋትም፤ የሕዝብህም ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። እንዲሁም በወይንህና በወይራህ አድርግ።
“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር በገባችሁ ጊዜ እኔ የምሰጣችሁ ምድር ታርፋለች፤ ለእግዚአብሔርም ሰንበት ታደርጋለች።