ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ አጥንቱንም ከእርሱ አትስበሩ፤ ከእርሱም እስከ ጥዋት የተረፈ ቢኖር በእሳት አቃጥሉት።
ዘሌዋውያን 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምትሠዉበት ቀንና በነጋው ይበላል፤ እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሥዋዕቱም ባቀረባችሁት ዕለት ወይም በማግስቱ ይበላ፤ እስከ ሦስተኛው ቀን የተረፈ ማንኛውም ነገር ይቃጠል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መሥዋዕታችሁን በሠዋችሁበት ዕለትና በማግስቱ ይበላል፤ እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ማናቸውም ነገር ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋውም እንስሳው በታረደበት ዕለት ወይም በማግስቱ መበላት አለበት፤ እስከ ሦስተኛው ቀን ተርፎ የቈየ ማናቸውም ሥጋ በእሳት ይቃጠል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምትሠውት ቀንና በነጋው ይበላል፤ እስከ ሦስተኛውም ቀን ድረስ ቢተርፍ በእሳት ይቃጠላል። |
ከእርሱም እስከ ጥዋት አንዳች አታስቀሩ፤ አጥንቱንም ከእርሱ አትስበሩ፤ ከእርሱም እስከ ጥዋት የተረፈ ቢኖር በእሳት አቃጥሉት።