በመታጠቂያም ታስታጥቃቸዋለህ፤ ቆብንም ታደርግላቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዐትም ክህነት ይሆንላቸዋል፤ እንዲሁም የአሮንንና የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ።
ዘሌዋውያን 16:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቀባውም፥ በአባቱም ፋንታ ካህን ሊሆን የሚካነው ካህን ያስተስርይ፤ የተቀደሰውንም የተልባ እግር ልብስ ይልበስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊቀ ካህናት ለመሆን አባቱን በመተካት የተቀባና የተሾመ ካህን ያስተስርይ፤ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአባቱም ፈንታ ካህን ሆኖ ለማገልገል ተለይቶ የሚቀባው ካህን የተቀደሰውን የበፍታ ልብስ ለብሶ ያስተስርያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአባቱ ምትክ ሊቀ ካህናት እንዲሆን ተለይቶ የሚሾመው ካህን የተቀደሰ የክህነት በፍታ ልብሱን ለብሶ ያስተሰርያል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቀባውም፥ በአባቱም ፈንታ ካህን ሊሆን የሚካነው ካህን ያስተስርይ፥ የተቀደሰውንም የበፍታ ልብስ ይልበስ፤ |
በመታጠቂያም ታስታጥቃቸዋለህ፤ ቆብንም ታደርግላቸዋለህ፤ ለዘለዓለም ሥርዐትም ክህነት ይሆንላቸዋል፤ እንዲሁም የአሮንንና የልጆቹን እጆች ትቀባቸዋለህ።
ለቅድስተ ቅዱሳንም ያስተስርይ፤ ለምስክሩ ድንኳን፥ ለመሠዊያውም ያስተስርይ፤ ለካህናቱም፥ ለጉባኤውም ሕዝብ ሁሉ ያስተስርይ።
የተቀደሰውንም የተልባ እግር ቀሚስ ይልበስ፤ የተልባ እግርም ሱሪ በገላው ላይ ይሁን፤ የተልባ እግር መታጠቂያ ይታጠቅ፤ የተልባ እግር አክሊልም በራሱ ላይ ያድርግ፤ እነዚህ የተቀደሱ ልብሶች ናቸው፤ ገላውንም በውኃ ታጥቦ ይልበሳቸው።
የተቀባውም ሊቀ ካህናት በሕዝቡ ላይ በደል እንዲቈጠርባቸው ኀጢአት ቢሠራ፥ ስለ ሠራው ስለ ኀጢአቱ ከመንጋው ነውር የሌለበትን ወይፈን ለእግዚአብሔር ለኀጢአት መሥዋዕት ያቀርበዋል።