ዘሌዋውያን 16:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፤ ሌላውንም ልብስ ለብሶ ይወጣል፤ የእርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ለካህናቱ እንዳስተሰረየ ለራሱም፥ ለሕዝቡም ያስተሰርያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተቀደሰውም ስፍራ ሰውነቱን በውሃ ይታጠብ፤ የዘወትር ልብሱንም ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ ለራሱ ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ፤ ለሕዝቡም ማስተስረያ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ይለብሳል፤ ወጥቶም ለእርሱ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕት እና ለሕዝቡ የሆነውን የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተቀደሰውም ቦታ ሰውነቱን ታጥቦ የዘወትር ልብሱን ይልበስ፤ ከዚያም ወጥቶ የራሱንና የሕዝቡን ኃጢአት ለማስተስረይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያቅርብ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተቀደሰውም ስፍራ ገላውን በውኃ ይታጠባል፥ ሌላውንም ልብስ ለብሶ ይወጣል፤ የእርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የሕዝቡንም የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፥ ለራሱም ለሕዝቡም ያስተሰርያል። |
ይህንም ሁሉ ወንድምህን አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን ታለብሳቸዋለህ፤ በክህነት እንዲያገለግሉኝ ትቀባቸዋለህ፤ እጆቻቸውንም ታነጻለህ፤ ትቀድሳቸውማለህ።
ካህናቱም በገቡ ጊዜ ከመቅደሱ በውጭው አደባባይ አይወጡም፤ የሚያገለግሉበትን ልብሳቸውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖሩታል፤ ሌላም ልብስ ለብሰው ወደ ሕዝብ ይወጣሉ።”
በሰባተኛውም ቀን ጠጕሩን ሁሉ ይላጫል፤ ራሱንም፥ ጢሙንም፥ ቅንድቡንም፥ የገላውንም ጠጕር ሁሉ ይላጫል፤ ልብሱንም፥ ገላውንም በውኃ ያጥባል፤ ንጹሕም ይሆናል።
ሙሴም አሮንን፥ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኀጢአትህን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፤ ለራስህና ለወገንህ አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቍርባን አቅርብ፤ አስተስርይላቸውም” አለው።
እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም፥ ስለ ልዩ ልዩ ጥምቀትም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዐቶች ብቻ ናቸው።