እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ ዞርሁ በድንኳኑም መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ እልልም አልሁለት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ እዘምርለትማለሁ።
ዘሌዋውያን 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከበታቹም ያለውን ነገር የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው፤ እነዚህንም ነገሮች የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ በውኃም ይታጠብ፤ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከበታቹ ያለውንም ነገር ሁሉ የነካ ማንም ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነዚህንም ነገሮች የሚያነሣ ማንም ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሰውነቱንም በውሃ ይታጠብ፤ እስከ ማታ ድረስ ግን ርኩስ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ከተቀመጠበት በታች ያለውን ማናቸውንም ነገር የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም እንደነዚህ ያሉ ነገሮችን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ በውኃም ይታጠባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈሳሽ ያለበት ሰው የተቀመጠበትን ዕቃ ሁሉ የሚነካ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል፤ ሰውየው የተቀመጠበትን ማንኛውንም ዕቃ የያዘ ልብሱን አጥቦ፥ ሰውነቱንም ታጥቦ፥ እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከበታቹም ያለውን ነገር የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው፤ እነዚህንም ነገሮች የሚያነሣ ልብሱን ይጠብ፥ በውኃም ይታጠብ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ነው። |
እነሆ፥ አሁን እግዚአብሔር በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ ዞርሁ በድንኳኑም መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ እልልም አልሁለት እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ እዘምርለትማለሁ።