ደዌው በታየበት ቀን ጤነኛው ቆዳ ርኩስ ይሆናል።
ነገር ግን ቍስሉ አመርቅዞ ቀይ ሥጋ ቢታይበት ርኩስ ይሁን።
የሚያዠው ሥጋ ግን ሲታይበት ርኩስ ይሆናል።
ነገር ግን በሥጋው ላይ የሚያዥ ቊስል ቢታይበት የረከሰ ይሆናል።
ካህኑም ያየዋል፤ እነሆም፥ በቆዳው ላይ ነጭ እባጭ ቢሆን፥ ጠጕሩም ተለውጦ ቢነጣ፥ ሥጋውም በእባጩ ውስጥ ቢያዥ፥
ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ለምጹ ቆዳውን ሁሉ ቢከድን የታመመውን ሰው፦ ካህኑ ‘ንጹሕ ነህ’ ይለዋል፤ ሁለመናው ተለውጦ ነጭ ሆኖአልና ንጹሕ ነው።
ካህኑም ጤነኛውን ቆዳ አይቶ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ ስለዚህ ለምጽ ነውና ርኩስ ነው።