ዘሌዋውያን 13:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለምጹም በቆዳው ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ለምጹም የታመመውን ሰው ቆዳውን ሁሉ ከራሱ እስከ እግሮቹ ድረስ እንደ ከደነው ለካህኑ ቢመስለው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደዌው በአካላቱ ሁሉ ላይ በመውጣት በሽተኛውን ከራስ ጠጕር እስከ እግር ጥፍር ያለበሰው መሆኑን ካህኑ እስካየ ድረስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለምጹም በቆዳው ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ካህኑ ማየት እስከሚችልበት አካል የለምጹ ደዌ የታመመውን ሰው ቆዳ ሁሉ ከራሱ እስከ እግሮቹ ድረስ ቢሸፍነው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ካህኑ አስተያየት የሥጋ ደዌው በሽታ ሰውየውን ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጒሩ የሸፈነው ከሆነ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለምጹም በቁርበቱ ላይ ሰፍቶ ቢወጣ፥ ለምጹም የታመመውን ሰው ቁርበቱን ሁሉ ከራሱ እስከ እግሮቹ ድረስ እንደ ከደነው ላካህኑ ቢመስለው፥ ካህኑ ያያል፤ |
“አንተ ስታስተምረኝ እኔ የምመልሰው ምን አለኝ? ይህንስ እየሰማሁ ከእግዚአብሔር ጋር እከራከር ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማኖር በቀር የምመልሰው ምንድን ነው?
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፤ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ በኀጢአታችን ምክንያት እንደ ቅጠል ረግፈናል፤ እንዲሁም ነፋስ ጠራርጎ ወስዶናል።
ካህኑ ያየዋል፤ እነሆም፥ ለምጹ ቆዳውን ሁሉ ቢከድን የታመመውን ሰው፦ ካህኑ ‘ንጹሕ ነህ’ ይለዋል፤ ሁለመናው ተለውጦ ነጭ ሆኖአልና ንጹሕ ነው።