ዘሌዋውያን 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፤ አንገቱንም ይቈርጠዋል፥ በመሠዊያውም ላይ ያኖረዋል። ደሙንም በመሠዊያው አጠገብ ያንጠፈጥፈዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑም ወደ መሠዊያው ያምጣው፤ ራሱን ቈልምሞ ይቀንጥሰው፤ የተቈረጠውንም ራስ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፍጠፍ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፤ ራሱንም ይቈለምመዋል፤ በመሠዊያውም ላይ ያቃጥለዋል። ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፈጠፋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑም ይህን ወፍ ተቀብሎ ወደ መሠዊያው በማቅረብ አንገቱን ይቈልምመው፤ በመሠዊያውም ላይ በሚገኘው እሳት ያቃጥለው፤ ደሙም በመሠዊያው ጐን ይንጠፍጠፍ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፥ ራሱንም ይቈለምመዋል፥ በመሠዊያውም ላይ ያቃጥለዋል። ደሙም በመሠዊያው አጠገብ ይንጠፈጠፋል፤ |
እግዚአብሔር ከግርፋቱ ያነጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢአት መሥዋዕትን ብታቀርቡ ሰውነታችሁ ረዥም ዕድሜ ያለውን ዘር ታያለች።
እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል፥ ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም፤ ነገር ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ፥ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ፥ እናንተንም እንዳስተማራችሁ፥ በእርሱ ኑሩ።