ሰቈቃወ 5:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከራብ የተነሣ ሰውነታችን ጠወለገ፤ ቍርበታችንም እንደ ምድጃ ጠቈረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቈዳችን እንደ ምድጃ ጠቍሯል፤ በራብም ተቃጥሏል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከራብ ጽናት የተነሣ ቆዳችን እንደ ምድጃ ጠቈረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ። |
ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፤ በመንገድም አልታወቁም፤ ቍርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፤ ደርቆአል፤ እንደ እንጨትም ሆኖአል።