ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር በቀርቀር ነበሩ፤ ሰይፍ የሚመዝዙ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና ከምሥራቅ ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ ዐሥራ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ።
መሳፍንት 8:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም የፋኑሄልን ሰዎች፥ “በደኅና በተመለስሁ ጊዜ ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ” ብሎ ተናገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም የጵኒኤልን ሰዎች፣ “በድል አድራጊነት በሰላም ስመለስ ከተማችሁን የምትጠብቁበትን ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም የጵኒኤልን ሰዎች፥ “በድል አድራጊነት በሰላም ስመለስ ከተማችሁን የምትጠብቁበትን ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እነርሱንም “ድልን ተቀዳጅቼ በሰላም እመለሳለሁ፤ በዚያን ጊዜ የከተማ መጠበቂያ ግንባችሁን አፈርሳለሁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም የጵኒኤልን ሰዎች ደግሞ፦ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ ይህን ግንብ አፈርሰዋለሁ ብሎ ተናገራቸው። |
ዛብሄልና ስልማናም ከሠራዊቶቻቸው ጋር በቀርቀር ነበሩ፤ ሰይፍ የሚመዝዙ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች ወድቀው ነበርና ከምሥራቅ ሰዎች ሠራዊት ሁሉ የቀሩ ዐሥራ አምስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ።