ስለዚህም የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን ሹልዳ አይበሉም፤ የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርቹን ሹልዳ አደንዝዞአልና።
መሳፍንት 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ወደ ፋኑሄል ወጣ፤ ለፋኑሄልም ሰዎች እንዲሁ አላቸው፤ የፋኑሄልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ጵኒኤል ሰዎች ሄዶ ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ የእነርሱም መልስ የሱኮት ሰዎች ከሰጡት መልስ ጋራ አንድ ዐይነት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ ጵኒኤል ሰዎች ሄዶ ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ የእነርሱም መልስ የሱኮት ሰዎች ከሰጡት መልስ ጋር ተመሳሳይ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌዴዎን ወደ ጵኑኤልም ሄዶ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ ነገር ግን የጵኑኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች የሰጡትን ተመሳሳይ መልስ ሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ወደ ጵኒኤል ወጣ፥ ለጵኒኤልም ሰዎች እንዲሁ አላቸው፥ የጵንኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለሱለት። |
ስለዚህም የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን ሹልዳ አይበሉም፤ የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርቹን ሹልዳ አደንዝዞአልና።
የእግዚአብሔር መልአክ አለ፥ “ሜሮዝን ርገሙ፤ ወደ እግዚአብሔር ርዳታ አልመጡምና፥ በኀያላን መካከል ወደ እርሱ ርዳታ አልመጡምና፥ በቤቶችዋ ያሉትን ሰዎች ፈጽማችሁ ርገሙ።”
እንጀራዬንና የወይን ጠጄን፥ ለሸላቾቼም ያረድሁትን ሥጋ ወስጄ ከወዴት እንደ ሆኑ ለማላውቃቸው ሰዎች እሰጣለሁን?”