La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መሳፍንት 8:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በኵ​ሩ​ንም ዮቶ​ርን፥ “ተነ​ሥ​ተህ ግደ​ላ​ቸው” አለው፤ ብላ​ቴ​ናው ግን ገና ትንሽ ነበ​ረና ስለ ፈራ ሰይ​ፉን አል​መ​ዘ​ዘም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ወደ በኵር ልጁ ወደ ዮቴር ዘወር ብሎ፣ “ግደላቸው” አለው፤ ዮቴር ግን ትንሽ ልጅ ነበርና ስለ ፈራ ሰይፉን አልመዘዘም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም የበኲር ልጁ ወደ ሆነው ዮቴር ዘወር ብሎ፥ “ግደላቸው” አለው፤ ዮቴር ግን ትንሽ ልጅ ነበርና ስለ ፈራ ሰይፉን አልመዘዘም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የበኲር ልጁን ዬቴርን “በል አሁን ግደላቸው!” ብሎ አዘዘው። ልጁ ግን ሰይፉን ሳይመዝ ቀረ፤ ገና ልጅ ስለ ነበር አመነታ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በኩሩንም ዬቴርን፦ ተነሥተህ ግደላቸው አለው፥ ብላቴናው ግን ገና ብላቴና ነበረና ስለ ፈራ ሰይፉን አልመዘዘም።

Ver Capítulo



መሳፍንት 8:20
5 Referencias Cruzadas  

የተ​ጻ​ፈ​ውን ፍርድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ያደ​ርግ ዘንድ። ይህች ክብር ለጻ​ድ​ቃኑ ሁሉ ናት።


እነ​ዚ​ያ​ንም ነገ​ሥት ወደ ኢያሱ ባመ​ጡ​አ​ቸው ጊዜ ኢያሱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የሄ​ዱ​ትን የተ​ዋ​ጊ​ዎ​ችን አለ​ቆች “ቅረቡ፤ በእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሥት አን​ገት ላይ እግ​ራ​ች​ሁን አኑሩ” አላ​ቸው። ቀረ​ቡም በአ​ን​ገ​ታ​ቸ​ውም ላይ እግ​ራ​ቸ​ውን አኖሩ።


ጌዴ​ዎ​ንም፥ “የእ​ናቴ ልጆች ወን​ድ​ሞቼ ነበሩ፤ አድ​ና​ች​ኋ​ቸው ቢሆን ኖሮ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ አል​ገ​ድ​ላ​ች​ሁም ነበር” አለ።


ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም፥ “ኀይ​ልህ እንደ ጐል​ማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነ​ሥ​ተህ ውደ​ቅ​ብን” አሉት። ጌዴ​ዎ​ንም ተነ​ሥቶ ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን ገደለ፤ በግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አን​ገት የነ​በ​ሩ​ትን ሥሉ​ሴ​ዎች ማረከ።


ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን፥ “ሰይ​ፍህ ሴቶ​ችን ልጆች አልባ እን​ዳ​ደ​ረ​ገ​ቻ​ቸው እን​ዲሁ እና​ትህ በሴ​ቶች መካ​ከል ልጅ አልባ ትሆ​ና​ለች” አለ፥ ሳሙ​ኤ​ልም አጋ​ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጌ​ል​ጌላ ወጋው።