አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
መሳፍንት 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባልንጀራውም መልሶ፥ “ይህ ነገር ከእስራኤል ሰው ከኢዮአስ ልጅ ከጌዴዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይደለም፤ እግዚአብሔር ምድያምንና ሠራዊቱን ሁሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶአል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጓደኛውም መልሶ፣ “ይህ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድያማውያንንና ሰፈሩን በሙሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶታልና” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጓደኛውም መልሶ፥ “ይህ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ እንጂ ሌላ ነገር ሊሆን አይችልም፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር ምድያማውያንንና ሰፈሩን በሙሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶታልና” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጓደኛውም “ይህማ የእስራኤላዊው የኢዮአስ ልጅ የጌዴዎን ሰይፍ ነው! ከቶ ሌላ ትርጒም ሊሰጠው አይችልም፤ እግዚአብሔር ለጌዴዎን በምድያምና በመላው ሠራዊታችን ላይ ድልን ሰጥቶታል!” ሲል መለሰለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባልንጀራውም መልሶ፦ ይህ ነገር ከእስራኤል ሰው ከኢዮአስ ልጅ ከጌዴዎን ሰይፍ በቀር ሌላ አይደለም፥ እግዚአብሔር ምድያምንና ሠራዊቱን ሁሉ በእጁ አሳልፎ ሰጥቶአል አለው። |
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
በለዓምም ባላቅን፥ “እነሆ፥ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፤ አሁን አንዳችን ነገር ለመናገር እችላለሁን? እግዚአብሔር በአፌ የሚያደርገውን ቃል እርሱን እናገራለሁ” አለው።
ኢያሱንም፥ “በእውነት እግዚአብሔር ሀገሩን ሁሉ በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶአል፤ በዚያች ምድር የሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ከእኛ የተነሣ ደነገጡ” አሉት።
ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፥ “እግዚአብሔር ምድሪቱን አሳልፎ እንደ ሰጣችሁ ዐወቅሁ፤ እግዚአብሔር እናንተን መፍራትን በላያችን አምጥትዋልና፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ የተነሣ ቀልጠዋልና።
እንዲህም ሆነ፤ በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር በኩል የነበሩት የአሞራውያን ነገሥት ሁሉ፥ በባሕሩም አጠገብ የነበሩ የፊኒቃውያን ነገሥት ሁሉ፥ እግዚአብሔር ከእስራኤል ልጆች ፊት የዮርዳኖስን ውኃ እስኪሻገሩ ድረስ እንዳደረቀ በሰሙ ጊዜ፥ ልባቸው ቀለጠ፤ ከእስራኤልም ልጆች የተነሣ አእምሮአቸውን ሳቱ።
እርሱም፥ “እግዚአብሔር አምላክ ጠላቶቻችንን ሞዓባውያንን በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ተከተሉኝ” አላቸው። ተከትለውትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓብም የሚያሻግረውን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እንዲያልፍ አልፈቀዱም።
ጌዴዎንም በደረሰ ጊዜ አንድ ሰው ሕልምን ለባልንጀራው ሲያጫውት፥ “እነሆ፥ ሕልም አለምሁ፤ እነሆም፥ አንዲት የገብስ እንጎቻ ወደ ምድያም ሰፈር ተንከባልላ ወረደች፤ ወደ ድንኳኑም ደርሳ እስኪወድቅ ድረስ መታችው፤ ገለበጠችውም፤ ድንኳኑም ወደቀ” ይል ነበር።
ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜዉን በሰማ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ፥ “እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ” አለ።
የሰፈሩም ሰዎች፦ ዮናታንንና ጋሻ ጃግሬውን “ወደ እኛ ውጡ፤ አንድ ነገርንም እንነግራችኋለን” አሉ። ዮናታንም ጋሻ ጃግሬውን “እግዚአብሔር በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ተከተለኝ” አለው።