መሳፍንት 5:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግሮችዋ አጠገብ ተደፋ፤ ወደቀ፤ ተኛ፤ በእግሮችዋ አጠገብ ተፈራገጠ፤ በተፈራገጠበትም በዚያ ተጐሳቍሎ ሞተ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤ በዚያም ተዘረረ፤ በእግሯ ሥር ተደፋ፤ ወደቀ፤ በተደፋበት በዚያ ወደቀ፤ ሞተም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግሮችዋ አጠገብ ተደፋ፥ ወደቀ፥ ተኛ፥ በእግሮችዋ አጠገብ ተደፋ፥ ወደቀ፥ በተደፋበት ስፍራ በዚያ ወድቆ ሞተ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግሮችዋ ሥር ተዝለፍልፎ ወደቀ፤ በእግሮችዋ ሥር ተደፋ፤ በወደቀበትም በዚያው ሞተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግሮችዋ አጠገብ ተደፋ፥ ወደቀ፥ ተኛ፥ በእግሮችዋ አጠገብ ተደፋ፥ ወደቀ፥ በተደፋበት ስፍራ በዚያ ወድቆ ሞተ። |
ግራ እጅዋን ወደ ካስማ፤ ቀኝ እጅዋንም ወደ ሠራተኛ መዶሻ አደረገች፤ በመዶሻውም ሲሣራን መታችው፤ ራሱንም ቸነከረች፤ ጆሮ ግንዱንም በሳች፤ ጐዳችውም።
የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በሰቅሰቅም ዘልቃ፦ ከሲሣራ የተመለሰ እንዳለ አየች፤ ስለምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች።