እነሆ፥ እኔ በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆችም ውኃን ሊቀዱ ይወጣሉ፤ ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ ስላት፥
መሳፍንት 4:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሲሣራም፥ “ጠምቶኛልና እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጪኝ” አላት፤ እርስዋም የወተቱን ዕቃ ፈትታ አጠጣችው፤ ፊቱንም ሸፈነችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲሣራም፣ “ጠምቶኛልና እባክሽን ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ እርሷም የወተት ዕቃውን ከፍታ የሚጠጣውን ሰጠችው፤ እንደ ገናም ሸፈነችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሲሣራም፥ “ጠምቶኛልና እባክሽን ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ እርሷም የወተት ጮጮውን ከፍታ የሚጠጣውን ሰጠችው፤ እንደገናም ሸፈነችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሲሣራም “እባክሽ የምጠጣው ውሃ ስጪኝ፤ በጣም ጠምቶኛል” አላት፤ እርስዋም ከቈዳ የተሠራውን የወተት ዕቃ ከፍታ አጠጣችውና እንደገና ሸፍና ደበቀችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ጠምቶኛልና እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጭኝ አላት፥ እርስዋም የወተቱን አቁማዳ ፈትታ አጠጣችው፥ ሸፈነችውም። |
እነሆ፥ እኔ በውኃው ጕድጓድ አጠገብ ቆሜአለሁ፤ የከተማዋ ሰዎች ሴቶች ልጆችም ውኃን ሊቀዱ ይወጣሉ፤ ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ ስላት፥
ተነሥቶም ወደ ሰራፕታ ሄደ፤ ወደ ከተማዪቱም በር በደረሰ ጊዜ አንዲት መበለት በዚያ እንጨት ትለቅም ነበር፤ ኤልያስም ጠርቶ፥ “የምጠጣው ጥቂት ውኃ በጽዋ ታመጭልኝ ዘንድ እለምንሻለሁ” አላት።
ድሆችና ምስኪኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያገኙምም፤ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እግዚአብሔር እሰማቸዋለሁ፤ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።
ኢያዔልም ሲሣራን ለመቀበል ወጥታ፥ “ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፤ አትፍራም” አለችው። ወደ እርስዋም ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ በምንጣፍም ሸፈነችው።
የቄናዊው የሔቤር ሚስት ኢያዔል፥ ከሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን፤ በድንኳን ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን።